የዲላ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች አዲስ ከተሾሙት የጌዳኦ ዞን አስተባባሪ አባላት ጋር ትውውቅ እና በቀጣይ ሊኖር በሚገባው የስራ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አደረጉ::

ዲዪ ጥቅምት 15/2014 ዓ.ም. (ህዝብ ግንኙነት) በቀጣይ አብሮ ለመስራትና ለመተዋወቅ በመገናኝታችንና ህዝብን ለማገልገል በመመረጣችሁ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና በራሴ ስም አንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ዶክተር ችሮታው አየለ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት አንድ ተቋም ከተቋቋመበት አካባቢና ማህበረሰብ ተለይቶ ምንም ስራ መስራት እንደማይችል ገልፀው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአከባቢው ማህበረሰብ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ሰፊ ስራ እየሰራ መቆየቱን ተናግረዋል::
አሁን ላይ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ስራ ከታች ከህብረተሰብ አንስተን በማየት በቀጣይ ምን እንስራ÷ የተጀመሩትን ስራዎችን እንዴት እናስቀጥል÷ አዲስ ምን እንሰራ ብለን አብረን በመናበብ ለመስራት ይህ የውይይት መድረክ ሰፊ ፋይዳ አለው ብለዋል::
አሁን የተገኝውን እድል በመጠቀም ህብረሰብን ለመጥቀም መስራት ይጠበቅብናል ያሉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዮት ደምሴ ወደ ኃላፊነት ከመጡ አጭር ቀናት መሆኑን ተናግረው ህዝብን ለማሻገር ምን መስራትና ከማን ጋር በመተጋገዝ መስራት እንዳለባቸው በማሰብ ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ መምጣታቸውን ገልፀው አሁን ላይ ተቋሙ እየሰራ ያለው ስራ የአከባቢውን ህዝብ አንድ እርምጃ እንድያሻግር ቀርቦ መወያየት በማስፈለጉ የተደረገ ውይይት ነው ብለዋል::
በቀጣይ የህብረተሰብ ችግር በቅርበት በመለየት እና በሚሰሩ ሥራዎች ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የህዝብን ለውጥ በሚያረጋግጡ የጋራ ግዳዮች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከመግባባት ተደርሷል::