ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የSTEM ምርምር ኮንፈረንስ መካሄድ ጀመረ። ዲ.ዩ ጥቅምት 19 ቀን 2014ዓ.ም (ህ.ግ)

በኮንፈረንሱ የSTEM ሴንተር በሀገር ደረጃም ሆነ በዩኒቨርሲቲው በቅርብ ጊዜያት የተጀመረ ቢሆንም ወደፊት በሳይንሳዊ ጥናት ለሀገራችን ዕድገትና ብልጽግና ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።
ኮንፈረንሱ "Challenges and prospects of STEAM Eduction in Ethiopia " በሚል መሪ ቃል ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በፕሮግራሙም የተለያዩ ጥናቶች ቀርበው ውይይት እንደሚካሄድባቸው ለማወቅ ተችሏል።
በዚህ በመጀመሪያው አገር አቀፍ የSTEM ምርምር ኮንፈረንስ ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር እንግዶች ፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ተመራማሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።