የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ካውንስል አባላት በጤና ሳይንሰ ኮሌጅና ሪፌራል ሆሰፒታል የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

ዲ.ዪ ጥቅምት 26/2014 ዓ.ም. (ህ.ግ.) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሪፌራል ሆስፒታል በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያሉበትን ተግዳሮቶች ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስል አባላት በማቅረብ ጉዳዩን በጥልቀት ለመረዳት ጉብኝት መደረጉ ተገለፀ፡፡
ይህ የመስክ ጉብኝት ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፌራል ሆስፒታል ያሉትን የአገልግሎት አሰጣጡን የለየና ለቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጠ እንደነበረ የገለፁልን የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ አሁን ግንባታ ላይ ያለው ህንፃ በታቀደለት ጊዜ አለማለቁ አሁን ላይ እየታዩ ላሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ተግዳሮቶች አገዛ እንዳለው ገልፀው በህንፃው ዙሪያ ከኮነትራክተሩ ጋር በመነጋገር የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበት ሂደት እንደተመቻቸ ተናግረዋል፡፡
አክለውም ዶ/ር ችሮታው በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ በዬዘርፉ ያሉ ችግሮችን በመለየት መፍትሄና አስተያየት የተሰጠ ሲሆን በውሃ ፍሳሽና በአነሰተኛ ጥገና ዙሪያ ያሉ ችግሮቾ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አቅጣጫ መቀመጡን ገልፀዋል፡፡
የህክምናና ተግባር ዋና ዳይሬክተር እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፌራል ሆስፒታል ም/ኘሬዝዳንት ተወካይ ዶ/ር ደረጀ ዳንኤል በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ያደረገው ጉብኝት እጅግ እንዳስደሰታቸው ገልፀው በሆስፒታላችን የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በቂ የሰው ኃይልና መሳሪያ ያለን ቢሆንም ከነባር ህንፃዎች ማርጀት ጋር ተያይዞ አሁን ካለው ተጠቃሚ ብዛት አኳያ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ተግዳሮት እንደገጠማቸው ተናግረዋል፡፡
ይህ አሁን ላይ ተጀምረው ያሉት አዳዲስ ህንፃዎች አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ እነኝህን ተግዳሮቶቻችንን በመቅረፍ የተሻለ አገልግሎት እንድንሰጥ ይረዳናል ብለዋል፡፡
የጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፌራል ሆሰፒታል ያለበትን ችግር የማኔጅመንት አባላት በአካል ተገኝተው ጉብኝት በማድረጋቸው መደሰታቸውን ገልፀው በማኔጅመንት በኩልና በኛ ሊፈቱ የሚገባቸውን በአስቸኳይ በመፍታት የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደሚቻል ተናግረዋል::