ዲላ ዪኒቨርሲቲ በአንድ ስማርት ካርድና ባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂን አካቶ የሚሰራ ማዕከላዊ የደህንነት አስተዳደር እና የተቀናጀ የመዳረሻ ቁጥጥር ስርዓት የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተደረገ::

ዲ.ዪ ህዳር 9/2014ዓ ም (ህዝብ ግንኙነት) ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የራሳቸውን ደህንነት ለማስጠበቅ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተቋማችን ወደዚህ ስርዓት መግባት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ያሉት ዶ/ር ችሮታው አየለ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት በግቢያችን የደህንነት ካሜራዎች በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ቢሆንም central security management and intgrated access control system ለመተግበር ባለፉት ወራት ሰፊ ሰራ መሰራቱን ተናግረዋል::
ለስራው የሚያስፈልጉ መረጃዎችን በመስጠት ክፍሎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበው ይህ የሚዘረጋው ስርዓት ተግባራዊ ሲሆን የተቋማችንን ደህንነትና ሰላማዊ የመማር ማስተማር አከባቢን ለመፍጠር ከማገዝ በላይ ማንኛውንም የደንበኞች መረጃ በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችልና ውጤታማነትን የሚጨምር ነው ብለዋል::
የመማር ማስተማሩን ሂደት በቴክኖሎጂ በተደገፈና ሰላማዊ ደህንነቱ የተጠበቀ ተቋም ለመመስረት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ተመሰገን ፍልጶስ የICT ዳሬክተር ይህ ኘሮጀክት በቀጣይ 6 ወራት የሚጠናቀቅ ሲሆን በአጠቃላይ 86 ሚልየን ብር እንደሚፈጅ ገልፀዋል::
እስካሁን ተቋማችን ይጠቀም የነበረው ባለ 1 GB ወጥ LAN አቅም ብቻ እንደነበረ ገልፀው ካለው ወቅታዊ የዘመናዊ መረጃ ፍላጎት አንጻር ይህ ኘሮጀክት ወደ ትግበራ ሲገባ በአጠቃላይ የተቋሙን ኔትወርክ አቅም ከእያንዳንዱ ህንጻ ወደ ዳታ ማዕከል ያለውን ግንኙነት ወደ 10GB እና ከካምፓስ ወደ ካምፓስ ያለው ግንኙነት ወደ 40GB ከፍ ያረገዋል ብለዋል::
የአዲስ system integration ስራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ጫኔ በበኩላቸው ይህ system ወደ ስራ ሲገባ የተቋሙን ሀብት ለመቆጣጠርና ሰራተኛውን ሆነ ተሽከራካሪዎችን ያለ ካርድ ወደ ግቢ የማያስገባና የማያስወጣ በመሆኑ የተቋሙን ደህንነት ለመጠበቅ ትልቅ እገዛ አለው ብለዋል::
አክለው አቶ ታምራት የመማር ማሰተማሩን ሆነ ተቋሙን ወደ ዘመናዊ ስርዓት ለማስገባት የሚዘረጋው system ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል::