የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከጌዴኦ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በልማት ስራዎች ዙሪያ ስያካሂድ የነበረውን ውይይት አቅጣጫ በማስቀመጥ አጠናቀቀ፡፡

የዚህ ዓይነቱ የውይይት መድረክ ባለፉት ግዜያት ለማካሄድ ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበረ የገለፁት ዶክተር ችሮታው አየለ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት  ከፍተኛ  የትምህርት ተቋማት ያሉበትን አከባቢ ማህበረሰብ በምርምር  በመደገፍ የማህበረሰብን ህይወት መቀየር ዋና መሪሃቸው መሆኑን ገልፀው እስካሁን በዞናችን ዘመናዊ የምርምር ውጤቶችን ከማዳረስ አኳያ እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ ከዞኑ አስተዳደር ጋር በማቀድ የማህበረሰብን የልማት ፍላጎት  ጥያቄ ለመመለሰ ከባለፈው ስራችን በበለጠ ለመሰራት ይህ መድረክ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለዞናችን ትልቁ ተቋማችን ነው ያሉን የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዮት  ደምሴ በበኩላቸው እሰካሁን የተሰሩት ስራዎች በርካታ ቢሆኑም አብሮ ተያይዞና አቅዶ የመስራት ረገድ ሰፊ ክፍተት መኖሩን ተናግረዋል፡፡

ይህ በአንዲህ እንዳለ የተጀመሩትን በማስቀጠል እና አዲሶችን አብሮ በማቀድ የማህበረሰብን የልማት ጥያቄ መመለስ ይቻላል ብለው በሪፌራል ሆስፒታል እየተነሱ ባሉ የስምና ደረጃ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ እንዳገኙ ገልጸው የሚነሱትን ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የየዘርፉ ኃላፊዎች መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡