የአንደኛ አመት የጋራ ኮርሳቸውን ላጠናቀቁ ተማሪዎች የትምህርት ክፍል ለመምረጥ የሚረዳ ገለፃ ተሰጠ

ዲ.ዩ፦ የካቲት 24/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና፣ ሐሴዴላ እና ኦዳያአ ግቢዎች የጋራ ኮርስ (Common Courses) ትምህርታቸውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ተማሪዎች የትምህርት ክፍሎችን መርጠው ለመቀላቀል የሚያስችል ገለጻ ተሰጥቷል።
በዩኒቨርሲቲው የፍሬሽማን ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዲን የሆኑት አስናቀ ይማም (ዶ/ር ) እንደተናገሩት ገለፃው ተማሪዎች የመጀመሪያ አመት ትምህርታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የተዘጋጀ ነው።
እንደ ዶ/ር አስናቀ ገለፃ ከሆነ ተማሪዎቹ የጋራ ኮርሶችን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ከመግባታቸው በፊት ምርጫቸውን በአግባቡ ለማስተካከል እንዲረዳቸው የወደፊት ሙያቸውን ስለሚወስኑ የትምህርት ክፍሎችና አይነቶች ቅድመ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ገለፃው ይረዳል።
ዶ/ር አስናቀ አክለውም፤ በዚህ መሠረት ኮሌጆች በስራቸው የሚገኙ የትምህርት ክፍሎችን ለተማሪዎች አስተዋውቀው ስለ ትምህርት ክፍሎቻቸውም የትኩረት መስክ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ ለተማሪዎቹ እንደሰጡ ተናግረዋል ።
ወንደሰን ገበያው (ዶ/ር)፣ የፍሬሽማን ኘሮግራም ተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ም/ዲን በተመሳሳይ፤ ተማሪዎች ስለ ነገ ህይወታቸው በማሰብ ዝንባሌአቸውን መሰረት አድርገው በመረጡት መስክ የትምህርት ክፍሎችን እንዲመርጡ ያግዛል ብለዋል። አክለውም ከዚህ በፊት በተለመደው መልኩ በቤተሰብም ሆነ በጓደኛ ተጽዕኖ ውስጥ ከሚደረጉ የትምህር ክፍል ምርጫዎች ነጻ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ገልጸዋል።
አቶ ኢሳያስ ይልማ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራር እና አልሙናይ ዳሬክተር በበኩላቸው፤ ይህን መሰል የገለጻ መርሃ-ግብር መዘጋጀት ተማሪዎች ስለሚገቡበት የትምህርት ክፍል የጠራ ግንዛቤ ይፈጥርላቸዋል ብለዋል።
አቶ አጥናፉ ግዛው፣ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ሶፍትዌር ልማት ቡድን መሪ በበኩላቸው፤ ተማሪዎች ምርጫቸውን ከንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በበይነ መረብ 'ኦንላይን' የሚያከናውኑ እንደመሆናቸው መጠን ስለ ምርጫቸው የተሻለ ግንዛቤ ኖሯቸው እንዲያከናውኑ ይህ ገለጻ መሰጠቱ ዘረፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
ገለጻውን ሲከታተሉ ያገኘናቸው ተማሪ ዮሴፍ ጎበና እና ትዕግስት ግርማ በበኩላቸው፤ በዚህ መልኩ ለተማሪዎች ገለጻ መሰጠቱ ስለ ትምህርት ክፍሎች በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ትምህርት ክፍሎችን እንዲለዩ ከማስቻሉም በላይ፤ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ እንዲያከናውኑ እንደሚረዳቸው ነግረውናል።
በሌላ መድረክ ገለጻውን የተከታተሉት ተማሪ ሳሙኤል ጉተማ እና ሴና ንዛም በበኩላቸው፤ ከዚህ በፊት ስለ ትምህርት ክፍሎች ምንም አይነት ግንዛቤ እንዳልነበራቸውና አሁን የትኛውን የትምህርት ክፍል መምረጥ እንዳለባቸው ገለጻው ግንዛቤ እንደሰጣቸው ነግረውናል።
የገለጻ መርሃግብሩ በሦስቱም ጊቢዎች (ሐሴዴላ፣ ኦዳያኣ፣ ዋና ግቢ) ለሚነኙ አንደኛ አመትን ላጠናቀቁ ተማሪዎች በተመሳሳይ መልኩ ተሰጥቷል። በቀጣይም ተማሪዎቹ በሚመርጧቸው የትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል።
..................
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
ተክክለኛ እና ወቅታዊ ተቋማዊ መረጃ ለማገኘት
#ቴሌግራም፦ University of the Green Land
ይከታተሉን!
ለጥያቄና አስተያየተዎ
#ኢሜይል፦ pirdir@du.edu.et

ይላኩል