በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ወስዳችሁ፣ በአቅም ማሻሻያ (remedial) ፕሮግራም ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡበት ቀን ከመጋቢት 14-15/2015 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን።
ስለሆነም በተጠቀሰው ጊዜ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ #ሐሴዴላ ግቢ እና በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ ደግሞ #ኦዳያአ ግቢ ሬጂስትራር ጽ/ቤት በአካል ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ትምህርት የሚጀመረው መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን።
ለምዝገባ ስትመጡ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ8ኛ ክፍሌ ካርድ ዋናውን እና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ፣ 3x4 የሆነ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡
#ማሳሰቢያ፦ ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም በአጠቃላይ ስድስት ሺህ ዘጠና አምስት (6,095) ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተምር ይሆናል።
 
ሬጂስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት
የዲላ ዩኒቨርሲቲ