

ዲ.ዩ መስከረም 02/2014 ዓም (ህ.ግ) ትልቁ ደስታና ዕርካታ የሰው ልጅን በመርዳት የሚገኘውን ውጤት ማየት ነው ያሉን ዶክተር ሰላማዊት አየለ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፌራል ሆስፒታል ም/ኘሬዝዳንት መላውን ሠራተኛ እንኳን ለ2014 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ ብለው የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሠራተኞች ከበጎ ፍቃደኛ ግለሰቦችና ተቋማት ጋር በመተባበር አዲሱን አመት በአዲስ ራዕይና በአዲስ ተግባር መጀመራቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል::
የአዲሱ ዓመት ክብረ በዓል ከታካሚዎች÷ ከጎዳና ልጆችና ከአቅመ ደካማ እናቶችና አባቶች ጋር በመሆን በሆስፒታል ቅጥር ግቢ የተከበረ ሲሆን በዕለቱም የተዘጋጀውን ማዕድ በጋራ በመቋደስና ለጎዳና ልጆች ከበጎ ፍቃደኞች የተሰበሰበውን ልብስ በማደል ተከብሮ መዋሉን ዶ/ር ሰላማዊት ገልፀዋል::
እንዲህ አይነት ተግባር በጥራትና ቁጥጥር ማሻሻያ ጽ/ቤት ከሚሰሩ የጥራት ለውጥ ሥራዎች አንዱ የሆነው የራህራሄና አክብሮት ህክምና (CRC) አገልግሎት አካል ነው ብለዋል::
ዲ.ዩ. ጳጉሜ 04 ቀን 2013 ዓ.ም (ሕ.ግ) የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት በማስተላለፍ ንግግራቸውን የጀመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ የበጎ ፈቃድ ሥራው በያዝነው ክረምት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ በመመደብ በወናጎ ወረዳ 7 ቤቶች እንዲሁም በዲላ ከተማ 6 ቤቶች በድምሩ 13 ቤቶችን በ15 ቀናት ውስጥ ለተቸገሩ ቤተሰቦች ገንብቶ በማስረከብ በኢኮኖሚ አቅማቸው የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ ታስቦ የተጀመረ ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለመርሃ ግብሩ መሳካት ድጋፍ ያደረጉትንና በዕለቱም ተገኝተው ሥራውን በጋራ ያስጀመሩትን የዲላ ከተማ እና የወናጎ ወረዳ አስተዳደር ካቢኔ አባላትን አመስግነው ቤት ለሚታደስላቸው ቤተሰቦችም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ ዶ/ር ችሮታው አያይዘውም እንዲህ ዓይነት ተግባር በቀጣይ አመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ዲ.ዩ ጳጉሜ 03/2013 ዓ.ም (ህ.ግ) በቀጣይ ሁለት ዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን እንተክላለን ያሉት በፕሮግራሙ የተገኙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ እንደ ሀገር “ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል በዚህ ዓመት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ፕሮግራም ዩኒቨርሲቲው በንቃት ሲሳተፍ መቆየቱን ገልፀው በዚህም 121 ሺህ ምግብ ነክ ያልሆኑ፣ 100 ቀርከሀ፣ 8040 ምግብ ነክ የሆኑ እና ተቋሙ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት የሚገኘው ምርጥ የቡና ዘር 247 ሺህ በአጠቃላይ ከ376,000 በላይ ችግኞችን በዩኒቨርሲቲው እና አካባቢው መተከሉን ተናግረዋል፡፡
ጌዴኦ እና አካባቢው አረንጓዴ እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም የበለጠ አልምተን ለሀገራችን አረንጓዴ አሻራ የማኖሩን ስራ በእጅጉ እናግዛለን ያሉት ዶ/ር ችሮታው ለቀጣይ ዓመት የሚተከሉ ችግኞችን የማፍላት ሥራ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አሳውቀዋል፡፡
Public and International Relations Directorate
P.O.Box: 419
E-mail: pirdir@du.edu.et
Phone: +251461310001
: +251463312459
Dilla University
University of the Green Land!
The website Developed by DUICT Business App Dev't