ዲላ ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የተገበራቸውን ፕሮጀክቶች መርቆ አስረከበ ዲ.ዩ፦ ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት በኩል የተገበራቸውን ፕሮጀክቶች የምረቅና ርክክብ መርሃግብር አካሄደ።
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞችን ተቀብሎ ለመፈተን ዝግጅቶች መጠናቀቃቸው ተገለፀ ዲ.ዩ፦ ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም(ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞችን ተቀብሎ ለማስፈተን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል። ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፤ እንደ ሀገር በተያዘው አቅጣጫ መሰረት ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች መሰጠቱ ኩረጃና ማጭበርበርን ለማስቀረት ወሳኝ ነው ብለዋል።
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ እና በሐሴዴላ ግቢ የተሰሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ተመረቁ ዲ,ዩ፦ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የከተማና መሰረት ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትርና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በተገኙበት፤ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል ነባር ህንፃዎች የሁለተኛ ዙር እድሳት የተጠናቀቁ እንዲሁም በሐሴዴላ ግቢ ዘመናዊ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ህንጻዎች ተመርቀዋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል ዲ,ዩ፦ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 1829 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በድምቀት አስመርቋል። ችሮታው አየለ (ዶ/ር )፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች፣ ለተመራቂ ወላጆች እንዲሁም ለተማሪዎች ለምረቃ መብቃት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
"ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ቃል የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የችግኝ ተከላ አካሄደ ዲ.ዩ፦ ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በአገርአቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው "ነገን ዛሬ እንትከል" የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካል የሆነ የችግኝ ተከላ በዲላ ዩኒቨርሲቲ እፅዋት ጥበቃና ኢኮቱሪዝም ማዕከል ከማለዳ ጀምሮ ተከናውኗል። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ጊዜያትም በደን ልማት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀው፣ በዛሬው እለት ከ17 ሽህ በላይ ችግኞችን በመትከል ላይ ነን ብለዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል በላብራቶሪ ዘርፍ የ"ISO" እውቅናን አገኘ ዲ.ዩ፦ ሐምሌ 09/11/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል በቲቢ ምርመራ(Gene xpert) ላብራቶሪ ዘርፍ በISO የጥራት ደረጃ መዳቢ ድርጅት የእውቅና ሰርቴፍኬት ማግኘቱ ተገለጸ።