የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከኘላን እና ልማት ሚንስቴር ጋር በመተባበር ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በኘሮጀክት ዝግጅት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ::

ዲ ዩ የካቲት 05/2014 ዓ ም (ህ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ያዘጋጁት የፕሮጀክት ዝግጅት ስልጠና ተጠናቀቀ።
የመንግስት ኘሮጀክቶችን ስርዓት ባለው መልኩ ለማስተዳደርና ለመቆጣጠር የሚያስችል ግንዛቤ መፍጠርን አላማ ያደረገው ስልጠና ሲካሄድ፣ ማንኛውም ኘሮጀክት የገንዘብ ፍቃድ ከማግኝቱ በፊት ነባራዊ ሁኔታው ተጠንቶ ዝርዝር ጉዳዮች መታየት እንዳለባቸው አፅንኦት ተሰጥቷል።
ኘሮጀክቶች ከመጀመራቸው በፊት እቅድና ሌሎች ተገቢ ጉዳዮች ቅድሚያ መታየት አለባቸው ያሉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ፣ የኘላን እና ልማት ሚንስቴር በኘሮጀክት ዝግጅት ዙሪያ ስልጠና መስጠቱም መንግስት ያስቀመጠውን መመሪያና ደንብ ለመተግበር ወሳኝ እንደሆነ አክለው ገልፀዋል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በአካል ጉዳተኝነት እና አካታችነት ላይ አተኩሮ ለአስተዳደር ሰራተኞች ሊሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ዲ፡ዩ የካቲት 4.2014 ዓ.ም /ህ.ግ/ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ ማዕከል ዳይሬክቶሬት እና የኢትዮጲያ አካል ጉዳተኞች ልማት ማሕበር በጋራ የአካል ጉዳተኞ እና አካታችነት ላይ አተኩረው ሲሰጡት የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ። በስልጠናው 30 ካምፓስ ፖሊስ አባላት እና 30 ከተለያዩ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ዘርፍ የተወጣጡ ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት ተሳትፈውበታል፡፡
ዶ/ር አባቡ ተሾመ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ማዕከል ዳይሬክተር እንደገለፁት አካል ጉዳተኞች የተመቻቸ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው እንደ ማንኛውም ሰው ሰኬታማ ስራዎችን ይከውናሉ።

ማስታወቂያ

ለድሀረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
...................................
የዲላ ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ2014 ሁለተኛ መንፈቀ ትምህርት አደረሳችሁ እያለ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ በተገለጹ የትምህርት ዓይነቶች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች አመልካቾቸን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡
........................................
አመልካቾች “Application Form” እና “Letter of Sponsorship” ከቴሌግራም ቻናላችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
*******************
Please trace our telegram channel for the original copy of the announcement.

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ወደናንተ የሚቀርበውን የሚዲያ አማራጭ በማስፋት ከኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ ጋር ተባብሮ በሳምንት አንድ ጊዜ ተቋማዊ ስራዎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በቋሚነት ይዞላችሁ ይመጣል፡፡

በመሆኑም ዘወትር ማክሰኞ የሚወጣውን እትም በመከታተል ተቋማዊ መረጃዎችን እንዲጋሩና በዩኒቨርሲቲው የልማት ሥራዎች ዙሪያ ገንቢ አስተያየትና ሃሳብ እንዲያካፍሉን ዩኒቨርሲቲው ይጋብዝዎታል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል በ2013 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ህ/ክ ጤና ቢሮ በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ባስመዘገበው ውጤት የላቀ አፈጻፀም እውቅና ተሰጠው፡፡

ዲ.ዩ. ታህሳስ 02/2014 ዓ.ም. (ህ.ግ) የጤና ተቋማት ዋና ዓላማቸው በሽታን መከላከልና መቆጣጠር መሆኑን የተረዳው የዲላ ዩኒቨርስቲ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ሆስፒታሉ በላቀ ውጤት አፈፃፀም በክልል ጤና ቢሮ መሰጠቱ የተቋማችንን ሠራተኞች ብሎም ክፍሎችን ለላቀ ስራ የሚያነሳሳ መሆኑን የተናገሩት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንሰ ኮሌጅና ሪፌራል ሆስፒታል የህክምናና ተግባር ስልጠና ዋና ዳሬክተር ዶክተር ደረጀ ዳንኤል ይህን እውቅና ለሠራተኛው ለማሳወቅና ተነሳሽነቱን ለማጎልበት ሲነር ማናጂመንት አባላት ልዩ መድረክ ማዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በፐብሊክና ዲጅታል ዲፕሎማሲ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደ።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፐብሊክ ዲፕሎማሲ የሚኖራቸው ሚና የላቀ በመሆኑ ምሁራን ቴክኖሎጂዎችን ሁሉ በመጠቀም ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ።

..............

ዲ.ዩ ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም(ህ.ግ) የሳይንስ ሳምንት አካል በሆነው በፓናል ውይይት ላይ የተገኙ እንግዶችንና ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተማ/አገ/ምክትል ፕሬዝዳንትና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ ይህ ወቅት መንግስት ለመንግስት ከሚያደርገው ዲፕሎማሲ ባሻገር ወደ ህዝብ ዲፕሎማሲ የተሻጋገርንበት ጊዜ በመሆኑ የህዝብ ዲፕሎማሲ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ይሁን እንጂ የህዝብ ዲፕሎማሲ ከሚሰጠው ጥቅም ባሻገር በጥንቃቄና በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ለአፍራሽ ተልዕኮ ሊውል እንደሚችል መገንዘብ እንዳለብን ተናግረዋል።

በሥነ-ምግባር የታነጸ አመራር ከሙስና የፅዳች ኢትዮጲያ›› በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ18 ግዜ በሀገራችን ለ17 ግዜ የፀረ-ሙስና ቀን በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ::

ዲ-ዩ -ህዳር 30/2014ዓ.ም (ህዝብ ግንኙነት) ሙስና የመንግስት እና የህዝብ ሀብት የግል ወይም የቡድን ፍላጎትን በህግ-ውጥ መንገድ ለግል ጥቅም ለሟሟላትና መልካም ስነ-ምግባር በሌላቸው ሰዎች የሚፈጸም፣ ተግባር፣ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ መብራቴ ሽፈራው የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክተር የሙስና መከሰት ዋነኛ መንስኤው የመልካም ስነ-ምግባር እሴቶች መሽርሸር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አክለውም ወ/ሮ ማብራቴ መልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲቀጭጭ የአገልግሎት አሰጣጡም ዜጎች በሚፈልጉት ደረጃ አንዳይሰጥ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ 16ተኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በፓናል ወይይትና በተለያዩ መርሃ ግብሮች በታላቅ ድምቀት አከበረ፡፡

ዲ.ዩ. ህዳር 29/2014 ዓ.ም. (ህ.ግ.) ህገ-መንግሰቱ የፀደቀበት ቀን የብ/ብ/ህ ቀን ሆኖ ተሰይሞ በየአመቱ እንዲከበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሚያዝያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም. መወሰኑን የተናገሩት ዶ/ር ችሮታው አየለ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት 'ወንድማማችነት ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነት' በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ የሚከበረው 16ተኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ልዩ የሚያደርገው ሀገር በህልውና ጦርነት ውስጥ ባለችበት ወቅት መሆኑና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የራሳቸውን ፍላጎትና የምዕራባዊያንን ተልዕኮ ለማሳካት ከተሰለፉ ጎራዎች ጋር የሚደረግ ጦርነት ላይ ባለንበት ወቅት መሆኑ ነው ብለዋል፡፡

Pages