የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከጌዴኦ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በልማት ስራዎች ዙሪያ ስያካሂድ የነበረውን ውይይት አቅጣጫ በማስቀመጥ አጠናቀቀ፡፡

የዚህ ዓይነቱ የውይይት መድረክ ባለፉት ግዜያት ለማካሄድ ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበረ የገለፁት ዶክተር ችሮታው አየለ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት  ከፍተኛ  የትምህርት ተቋማት ያሉበትን አከባቢ ማህበረሰብ በምርምር  በመደገፍ የማህበረሰብን ህይወት መቀየር ዋና መሪሃቸው መሆኑን ገልፀው እስካሁን በዞናችን ዘመናዊ የምርምር ውጤቶችን ከማዳረስ አኳያ እየተሰራ ያለው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ ከዞኑ አስተዳደር ጋር በማቀድ የማህበረሰብን የልማት ፍላጎት  ጥያቄ ለመመለሰ ከባለፈው ስራችን በበለጠ ለመሰራት ይህ መድረክ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለዞናችን ትልቁ ተቋማችን ነው ያሉን የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዮት  ደምሴ በበኩላቸው እሰካሁን የተሰሩት ስራዎች በርካታ ቢሆኑም አብሮ ተያይዞና አቅዶ የመስራት ረገድ ሰፊ ክፍተት መኖሩን ተናግረዋል፡፡

DU 3rd Science Week

"Science for Public and Digital Diplomacy"
08-10 December, 2021.
..............
We feel a great honor to invite you all to participate and take part in the 3rd Science Week to be celebrated at Dilla University with a series of science-related events for the general public from 08-10 December 2021.
It is a national program celebrated every November as part of “Building Science Culture”.

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከUNHCR ጋር በመተባበር በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዙሪያ ያዘጋጀው ስልጠና በይርጋጨፌ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

ዲ.ዩ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም (ህ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህግና አስተዳደር ጥናቶች ኮሌጅ ከUNHCR ጋር በመተባበር በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መሠረታዊ መብት እና የሀገራት ግዴታ ዙሪያ በይርጋጨፌ ከተማ ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጠ።
በስልጠናው ላይ የተሳተፉ እንግዶችና ባለድርሻ አካላትን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህግና አስተዳደር ጥናቶች ኮሌጅ በምርምር ዘርፍ ምክትል ዲን አቶ ተካልኝ ዱጌ ስልጠናው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት እንደሆነ ገልጸው በስልጠናውም የተፈናቃዮች መብቶች ምንድ ናቸው? የመንግስታትስ ግዴታስ ምንድነው? ተቋማትስ ለተጎጆዎች የሚያደርጉት ክትትልና ድጋፍ ምን መምሰል አለበት? የሚሉ ሃሳቦችን በስፋት ለማንሳትና ለችግሮቹም በጋራ መፍትሔ ለመስጠት እንደታሰበ ገልጸዋል።

ዲላ ዪኒቨርሲቲ በአንድ ስማርት ካርድና ባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂን አካቶ የሚሰራ ማዕከላዊ የደህንነት አስተዳደር እና የተቀናጀ የመዳረሻ ቁጥጥር ስርዓት የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተደረገ::

ዲ.ዪ ህዳር 9/2014ዓ ም (ህዝብ ግንኙነት) ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የራሳቸውን ደህንነት ለማስጠበቅ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተቋማችን ወደዚህ ስርዓት መግባት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ያሉት ዶ/ር ችሮታው አየለ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት በግቢያችን የደህንነት ካሜራዎች በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ቢሆንም central security management and intgrated access control system ለመተግበር ባለፉት ወራት ሰፊ ሰራ መሰራቱን ተናግረዋል::
ለስራው የሚያስፈልጉ መረጃዎችን በመስጠት ክፍሎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበው ይህ የሚዘረጋው ስርዓት ተግባራዊ ሲሆን የተቋማችንን ደህንነትና ሰላማዊ የመማር ማስተማር አከባቢን ለመፍጠር ከማገዝ በላይ ማንኛውንም የደንበኞች መረጃ በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችልና ውጤታማነትን የሚጨምር ነው ብለዋል::

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

ዲ.ዩ ህዳር 6 ቀን 2014 ዓ.ም (ህ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ያሰባሰበውን ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አስረከበ።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተደረገውን ድጋፍ ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም የሀገርን ህልውና ለማስከበር ግዳጅ ላይ መስዋህትነትን እየከፈለ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት 3 ሚሊየን ብር በመለገስ አጋርነቱን ማሳየቱን ገልጸው ዛሬ ደግሞ ከዩኒቨርሲቲው ካፒታል በጀት 2 ሚሊዮን ድጋፍ እና ከሰራተኞች የወር ደሞዝ የተሰበሰበን በድምሩ 30 ሚሊዮን ብር እና በአይነት 200 ፍራሽ እንዲሁም 100 ተደራራቢ የብረት አልጋ ድጋፍ ማደረጉን ተናግረዋል ።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ዲዩ ህዳር 02/2014 ዓ.ም (ህዝብ ግንኙነት) ተቋማችን ከአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የተመደበ በመሆኑ በተግባር ትምህርት እጃቸውን የፈቱ ሙሩቃንን ለማፍራት ቆርጦ እየሠራ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ደረጀ ክፍሌ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምር/ቴክ/ሽግ/ምክ/ፕሬዝዳንት ተወካይ ከተቋማት ጋር የሚኖረን ትስስር በእጅጉ የጠበቀ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት ስርዓተ ትምህርት ሲቀረፅ የኢንዲስትሪዎችን ፍላጎት ያገናዘበ እንዳልነበረ ተናግረው አሁን ላይ ከተለያዩ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎች ፍላጎት እና የስራ እድል ከማስገኘት አኳያ ስርዓተ ትምህርት እየተቀረፀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ደረጀ አክለውም የደቡብ ሬድዮና ቴሌቭዝን ድርጅት ባለው ቴክኖሎጂ በመታገዝ እኛጋ ያለውን ዕውቀት በማስተሳሰር በክህሎቱ የተሻለ ዜጋ ለመፍጠር ይህን የመሰለ ስምምነት መፍጠራችን እገዛው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

ከጌዴኦ ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች ለተወጣጡ እናቶች ማገዶ ቆጣቢ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ የግንዛቤና የተግባር ስልጠና ተሰጠ።

ዲ.ዩ ህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም (ህ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ስርጸት ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ከጌዴኦ ዞን ከኮቸሬ፣ ከይርጋጨፌ፣ ከወናጎ እና ከዲላ ዙሪያ ወረዳዎች ለተውጣጡ እናቶች ማገዶ ቆጣቢ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ ስልጠና ሰጠ። ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት በሚገኝበት አካባቢ ላይ የሀይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂ ላይ መስራት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የተናገሩት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ስርጸት ዳይሬክቶሬት ዶ/ር ሀብታሙ ተመስገን ስልጠናው የኖሮዌይ መንግስት ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር ለመስራት በተስማማው መሰረት በትብብር የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ ገልጸው በስልጠናው ከዚህ ቀደም ማገዶ ቆጣቢ ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ፣ በማኅበር ተደራጅተው በመስራት አምርተው የሚሸጡ፣ ባዮጋዝና ሶላር ኢነርጂን የሚጠቀሙ አዲስ እና ነባር ወደ 40 የሚደርሱ እናቶች መሳተፋቸውን ገልጸው በቀጣይ ሌሎች ወረዳዎችንም ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ዶ/ር ሀብታሙ አክለውም የዲላ ዩኒቨርሲቲ የዚህ አይነት የትብብር ስራዎች ላይ በሩን ክፍት አድርጎ በመስራቱ እና ባለ

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ካውንስል አባላት በጤና ሳይንሰ ኮሌጅና ሪፌራል ሆሰፒታል የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡

ዲ.ዪ ጥቅምት 26/2014 ዓ.ም. (ህ.ግ.) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሪፌራል ሆስፒታል በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያሉበትን ተግዳሮቶች ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስል አባላት በማቅረብ ጉዳዩን በጥልቀት ለመረዳት ጉብኝት መደረጉ ተገለፀ፡፡
ይህ የመስክ ጉብኝት ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፌራል ሆስፒታል ያሉትን የአገልግሎት አሰጣጡን የለየና ለቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጠ እንደነበረ የገለፁልን የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ አሁን ግንባታ ላይ ያለው ህንፃ በታቀደለት ጊዜ አለማለቁ አሁን ላይ እየታዩ ላሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ተግዳሮቶች አገዛ እንዳለው ገልፀው በህንፃው ዙሪያ ከኮነትራክተሩ ጋር በመነጋገር የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበት ሂደት እንደተመቻቸ ተናግረዋል፡፡

Pages