የዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብን ችግር በዘላቅነት ለመፍታት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ዲ.ዩ. ጥቅምት 07/2014 ዓ.ም. (ህ.ግ.) ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተቋቋሙበት አከባቢ ያለውን የማህበረሰቡን ችግሮች በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት መፍታት አንዱ የስራቸው አካል መሆኑን የተናገሩት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ኘሬዝዳንት ተወካይ ዶክተር ደረጄ ክፍሌ በይርጋጨፌና ኮቾሬ ወረዳዎች የደረሰውን የጎርፍ አደጋ አጥኝ በመመደብ የችግሩን መጠን በዝርዝር ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስል በማቅረብና ችግሩን በዘላቅነት ለማስቀረት ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ዛሬ በኮቾሬ ተገኝተው ድጋፉን በሚያበረክቱበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር አሰራርን ለማዘመን ስልጠና ተሰጠ::

ዲ.ዩ. ጥቅምት 6 ቀን 2014 ዓ.ም (ሕ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከፌዴራል መንግስት የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የግዥ አጽዳቂ ኮሚቴዎችና ከተለያዩ የሥራ ክፍል ለተወጣጡ ባለሙያዎች በመንግስት ግዥ አስተዳደር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በስልጠናው ፕሮግራም ላይ የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ የተቀላጠፈ አሰራር በተቋም ደረጃ ለማረጋገጥ ስልጠናው በክህሎትና በዕውቀት ደረጃ ግንዛቤ ለማስጨበጥ አሰፈላጊ መሆኑን ገልፀው እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የግዥና ንብረት አስተዳደር አሰራር ሥርዓትን ዘመናዊ ለማድረግ ደንቦች፣ ሕጎችንና መመሪያዎች ተከትለን መሥራትና አሰራሩን ቀልጣፋ ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡

14ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዲላ ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ተከበረ።

ዲ.ዩ ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም (ህ.ግ) 14ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን "በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉዓላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ" በሚል መሪ ቃል በዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከበረ።
በአገራችን አዲስ ካቢኔ ተዋቅሮ መንግስት በይፋ ስራ የጀመረበት ወር ላይ ይህን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ማክበራችን ልዩ ያደርገዋል ያሉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሎታው አየለ ይህ ክቡር የሆነ ሰንደቅ ዓላማ በግዑዝ ሲታይ ከጨርቅ የተሰራ ይሁን እንጂ ውስጠ ሚስጥሩ ግን የኢትዮጵያ ማንነት መገለጫ የሆነ ብዝዎች የተሰውለት እና ብዝዎች ውድ ዋጋ የከፈሉለት ምልክት ከመሆኑም በላይ ለብዙ የአፍሪካ አገራት ጭምር ብሔራዊ ባንዲራ ሆኖ በማገልገል ላይ ያለ ሰንደቅ ዓላማ እንደሆነ ተናግረዋል ።

የኢትዮጰያ አካል ጉዳተኞች ልማት ማዕከል ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ ማዕከል ከ140, 000 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ ለአካል ጉዳተኞች የትምህርት መርጃ ቁሳቁሰ ድጋፍ አደረገ::

ዲ.ዩ. መስከረም 28/2014 ዓ.ም (ህ.ግ) ድርጅቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት በአካል ጉዳተኞች ላይ ድጋፍ በማድረግ እየሰራ እንደቆየ ያስታወሱት ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስ/ተማ/አገ/ምክ/ኘሬዝዳንት ለአካል ጉዳተኞች ስልጠናና ድጋፍ ከመስጠት አልፎ ለሌላው ማህበረሰብ በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጡን ስራ በሰፊው መስራቱን ተናግረዋል::
ዶ/ር ዳዊት አክለው ድርጅቱ የተቋማችን አጋር በመሆን በተለይ አካል ጉዳተኞችን በግብዓት በመደገፍ ሰፊ ስራ እየሠራ ነው ብለዋል::

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ3ኛ (PhD) እና የ2ኛ ዲግሪ የአዲስ ስርዓተ ትምህርቶች ግምገማ አውደ- ጥናት አካሄደ።

ዲ.ዩ መስከረም 22 ቀን 2014 ዓ.ም (ህ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የስርዓተ ትምህርቶች የውስጥ እና የውጪ ግምገማ አውደ -ጥናት አካሄደ።
ወደ አውደ-ጥናቱ የመጡ እንግዶችና ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክ እና ምርምር ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት መላኩ አውደ-ጥናቱ ለኮሌጁ የመጀመሪያው የሆነውን የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም በሕብረተሰብ ጤና (PhD in Public Health) እና ለኮሌጁ 5ተኛ የሆነውን የ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራም በአካባቢ ጤና (MPH in Environmental Health) ለመክፈት የተደረገ የካሪኩለሞች ግምገማ አውደ ጥናት መሆኑን አስታውቀዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ዶ/ር አበባየሁ ታደሴ እና ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ አዲስ በተዋቀረው በደብብሕክ መንግስት ምስረታ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ሆነው ተሾሙ::

ዛሬ በተዋቀረው በደብብሕክ የመንግስት ምስረታ ላይ የክልሉ አፌ-ጉባኤ እና ምክትል አፌ-ጉባኤ እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሾሙ የሚታወቅ ሲሆን በርዕሰ መስተዳድሩ የተከበሩ አቶ ርስቱ ይርዳው አቅራብነት የክልሉ ካቢኔ አባላትና የፌደሬሽን ምክር ቤት ተወካዮች ተሰይመዋል::
ከዕጩዎች መካከል የዩኒቨርሲቲያችን የምርመርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት እና የብልፅግና ፓርቲ ተወካይ ዶ/ር አበባየሁ ታደሴ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ እና የዩኒቨርሲቲያችን የሀገር በቀል ጥናት ተቋም (Indigenous Institute) ኃላፊ እና የኢዜማ ፓርቲ ተወካይ ዶ/ር ኦንጋዬ ኦዳ የክልሉ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል::

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ለኮቪድ-19 ሕክምና አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን Heart to Heart International ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በድጋፍ መልክ አገኘ::

ዲ.ዩ. መስከረም 22 2014 ዓ.ም. የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሪፌራል ሆስፒታል በአሜሪካን ሀገር በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከተቋቋመው Heart to Heart International ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለኮቪድ-19 ሕክምና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶችን ድጋፍ እንደተደረገለት የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፌራል ሆስፒታል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሰላማዊት አየለ ገልጸዋል፡፡
ድጋፍ የተደረጉት ዕቃዎች በገንዘብ ስሰላ 5,030 የአሜሪካን ዶላር ማለትም ብር 231,000 ዋጋ የሚያወጡና የኮቪድ-19 ህክምና ላይ ለምንሰራቸው ስራዎች ጉልህ አስተዋጽኦ ያላቸው የህክምና ግብዓቶች መሆናቸውን ዶ/ር ሰላማዊት ተናግረው ለጠቋማችን ተልዕኮ ስኬት ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሚደረጉ ትብብሮች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት በ2013 ዓ.ም. ዕቅድ አፈፃፀም እና በ2014 ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

ዲ.ዩ. መሰከረም 20/2014 ዓ.ም. (ህ.ግ) በተቋማችን ያሉ ችግሮችን ሆነ ጠንካራ ስራዎችን አውጥተን ተነጋግረን ለድክመቶቻችን መፍትሄ÷ ጠንካራ ጎናቻችንን ደግሞ ለማስቀጠል የካውስል አባላት ሚና የጎላ ነው ያሉን የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ ባለፉት ግዜያት ከካውሰል አባላት ጋር ለመገናኝትና ለመወያየት የኮቭድ-19 ተጽዕኖ ትልቅ ተግዳሮት እንደነበረ ተናግረዋል፡፡ የዬዘርፉ ኃላፊዎች ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በየክፍሉ የተሰሩትንና ልሰሩ የታቀዱትን በሪፖርት አቅርበዋል፡፡ እንዲሁም በዬዘርፉ በበጀት ዓመቱ መልካም ተሞክሮዎችና ስኬቶችም የተዳሰሱ ሲሆን ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች ተብራርተዋል፡፡ የካውንስል አባላቱም በሪፖርት አቀራረብ መደሰታቸውን ገልፀው የተለያዩ ጥያቄዎችን ለየዘርፍ ኃላፊዎች አቅርበው ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን በ2014 የበጀት ዓመት የተሳካ ስራ ለመስራት ተነጋግረዋል፡፡

ዲላ ዩኒቨርሲቲ "ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት" ሃገራዊ ዘመቻን ተቀላቀለ።

ዲ.ዩ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም (ህ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ የ"ነጩ ፓስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት" ዘመቻ መቀላቀሉን መልዕክት በማስተላለፍ ንግግራቸውን የጀመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሎታው አየለ ይህ ሃገራዊ ዘመቻ የአሜሪካ መንግስት ይልቁንም ፕሬዝዳንቱ ሀገራችን ላይ የሚያደርጉትን ፍታዊ ያልሆነ ጫና እንዲቀንሱና ከእኛ ላይም እጃቸውን እንዲያነሱ ለማድረግ ታስቦ የተጀመረ ሃገራዊ ዘመቻ መሆኑን ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከዚህ ቀደም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም በማስከበር ግዳጅ ላይ መስዋህትነት እየከፈለ ለሚገኘው የሀገር መከላኪያ ሠራዊት 30 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ድጋፍ በመለገሰ አጋርነቱን ማሳየቱን ገልጸው በቀጣይ ሳምንት ደግሞ ለተፈናቀሉ ወገኖች በአይነት ድጋፍ ለማድረግ እንደ ተቋም ዕቅድ መያዙን ገልፀዋል።

Pages