ህወሓት በከፈተው ጦርነት የሀገርን ጥሪ ተቀብለው ለሙያዊ አገልግሎት የዘመቱ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ባለሙያዎች ግዳጃቸውን አጠናቀው ተመለሱ

ዲ.ዩ፡- ግንቦት 8/2014ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) ህወሓት በከፈተው ጦርነት የሀገርን ጥሪ ተቀብለው ለሙያዊ አገልግሎት የዘመቱ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ባለሙያዎች ግዳጃቸውን  አጠናቀው ተመለሱ፡፡ ባለሙያዎቹ ህወሓት ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ሰርጎ በመግባት በፈፀመው ወረራ ወቅት ወረራውን ለመመከት በተካሄደው ሀገራዊ የዘመቻ ተሳትፎ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ሄዱው እንደ ነበር የሚታወስ ነው፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ዘማች ባለሙያዎቹን እንኳን በደህና መጣችሁ ባሉበት ንግግራቸው ሀገርና ህዝብ የሰጧችውን ኃላፊነት በጀግንነት ፈፅመው  በመመለሳችው "ትልቅ ኩራት ተሰምቶናል" ብለዋል፡፡ ዶ/ር ችሮታው አክለውም ግዳጃችሁን በሚገባ በማከናወናችሁ ለበርካቶች አርአያ የሚሆን የጀግንነት ስራ ሰርታችኋል ስለሆነም ተቋሙ ማንኛውንም የእናንተን ጥቅማጥቅም የሚያሟላ ይሆናል ነው ያሉት፡፡

Announcement

Call for Research Project Proposal, 2022/23. ....... Dilla University, Research and Dissemination Directorate, have released the call for the 2022/23 research project proposal, for all grant types. 

Any interested DU academic staff and affiliates are highly welcomed to apply under the state of carry-on presented below.

በምርምር የለሙ የቡና ችግኞችን ለአርሶ አደሮች ማሰራጨቱን ዲላ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ

ዲ.ዩ፦ ሚያዝያ 25/2014 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) በምርምር የለሙ የቡና ችግኞችን ለአርሶ አደሮች ማሰራጨቱን ዲላ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ በይርጋጨፌ ወረዳ ዱመርሶ ቀበሌ ችግኝ ጣብያ ማዕከል እና በኮቾሬ ወረዳ የችግኝ ልማት ቦታዎች ተፈልተው ለተከላ ዝግጁ የሆኑ የቡና ችግኞችን ለአርሶ አደሮች ማሰራጨቱን የገለፀው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ነው፡፡ የቡና ችግኞቹ የተሰራጩት በወረዳዎቹ ለተመረጡ አርሶ አደሮች መሆኑንም ዳይሬክቶሬቱ አክሎ ገልጿል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ አዳዲስ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር የትውውቅ እና የውይይት መርሐ- ግብር አካሄዱ።

ዲ.ዩ ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ( ህ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት በአዲስ መልክ መዋቀሩ የሚታወቅ ሲሆን በምደባው መሠረትም፣
1. ዶ /ር መለሰ መኮንን ሰብሳቢ
2. ፕ/ር አለማየሁ ጫላ ም/ ሰብሳቢ
3. አቶ አብዮት ደምሴ አባል
4. ወ/ሮ ሳራ ይርጋ አባል
5. ዲ/ን ዳንኤል ክብረት አባል
6. ዶ/ር አዱኛ ደበላ አባል
7. ዶ/ር ፍቃዱ ጉርሙ አባል
ሆነው እንዲሰሩ ከሚያዚያ 2014 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ችግኞችን ለአርሶ አደሮች ማሰራጨቱን አስታወቀ

ዲ.ዩ፦ ሚያዚያ 20/2014 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ችግኞችን ለአርሶ አደሮች ማሰራጨቱን አስታወቀ። በተያዘው 2014 ዓ.ም በተለያዩ የችግኝ ልማት ቦታዎች ተፈልተው ለተከላ ዝግጁ የሆኑ የቡና ችግኞችን ለአርሶ አደሮች ማሰራጨቱን የገለፀው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሮክተሬት ነው።
በዲላ ዙሪያ ወረዳ ጪጩ ችግኝ ጣቢያ ማዕከል እና በአባያ ወረዳ ሰመሮ የቡና ችግኝ ጣቢያ የለሙ ችግኞች ለተመረጡ አርሶ አደሮች መሰራጨተውን ነው ዳይሬክቶሬቱ አክሎ የገለፀው፡፡

የአሜሪካ ኮንግረስ በኢትዮጲያ ላይ እንዲተገበር ያዘጋጀው 'H.R 6600’ ረቂቅ ሰነድ የኢትዮጵያን ህዝብ ለዘርፈ-ብዙ ጉዳት የሚዳርግ መሆኑ ተገለፀ

ዲ.ዩ መጋቢት 20/2014 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የአሜሪካ ኮንግረስ በኢትዮጵያ ላይ እንዲተገበር ያዘጋጀው የ'H.R 6600’ ረቂቅ ሰነድ የኢትዮጵያን ህዝብ ለዘርፈ-ብዙ ጉዳት የሚዳርግ መሆኑ ተገለፀ። ኢትዮጵያ ወታደራዊ ቁሳቁስ እንዳትሸምት፣ የብድር እና ምጣኔ ሀብት ድጋፍ እንዳታገኝ፣ በውጭ ከሚኖሩ ዲያስፖራዎቿ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ፍሰት (ሬሚታንስ) እንዲቋረጥ፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉ ተቋማትና መንግስታት ሳይቀር የዲፕሎማሲ መገለል እንዲደረግባት የማዕቀብ ረቂቅ አንቀፆች የተካተቱበት ይህ የኮንግረስ ሰነድ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት በፊርማቸው እንዲተገብሩት ፈላጭ ቆራጭ ስልጣን ሰጥቷቸዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ለተውጣጡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ

ዲ.ዩ መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ለተውጣጡ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ። የዲላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ ማዕከል ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ልማት ማዕከል ጋር በመተባበር ነው ስልጠናው የተሰጠው። ሰልጣኞቹ ከተለያዩ ትምህርት ክፍሎች የተወጣጡ 25 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሲሆኑ ለሁለት ቀናት በህይወት ክህሎት ዙሪያ የግንዛቤ ስልጠና ነው እየተሰጣቸው።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር አባቡ ተሾመ ጽ/ቤታቸው ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ለመምህራን፣ ለአስተዳደር ሰራተኞች፣ ለተማሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል። የአሁኑ ስልጠናም ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ልማት ማዕከል ጋር በትብብር እየተሰጠ መሆኑን አክለው ገልፀዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ በቨርሚ ኮምፖስት የአፈር ማዳበሪያ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ ለአርሶ አደሮች የቴክኖሎጂ ሽግግር ስልጠና ሰጠ

ዲ.ዩ መጋቢት 17 ቀን 2014 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ በቨርሚ ኮምፖስት የአፋር ማዳበሪያ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ ለአርሶ አደሮች የቴክኖሎጂ ሽግግር ስልጠና ሰጠ። የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት በወናጎ እና አባያ ወረዳ ለሚገኙ ሞዴል አርሶ አደሮች ነው ስልጠናውን የሰጠው። ስልጠናው ለ2ተኛ ዙር የተዘጋጀ የተግባር ተኮር እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መሆኑን ዳይሬክተሬቱ ገልፀዋል።
የቨርሚ ኮምፖስት ፕሮጀክት በአካባቢው ላይ በሂደት የተፈጠረውን የአፈር ለምነት ችግር ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ መልሶ ለማምጣት ታልሞ የተጀመረ ፕሮጀክት እንደሆነ በስልጠናው ላይ ተገልጿል። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክተር አቶ ክብሩ አለሙ በስልጠናው ከዚህ በፊት ሰልጥነው ማሳቸው ላይ ጥሩ ተሞክሮ አድርገው ለውጥ ያሳዩ ሰልጣኞችን ጨምሮ ወደ 40 የሚደርሱ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን ገልጸዋል።

የፌዴራል የፍትሕና የህግ ኢንስቲትዩት ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ህግ ት/ቤት የመጻሕፍት ድጋፍ አደረገ።

መጋቢት 16 ቀን 2014 ዓ.ም (ህ.ግ) የፌዴራል የፍትሕና የህግ ኢንስቲትዩት ለህግ ትምህርት የሚያገለግሉ አጋዥ መፃህፍትን ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት ድጋፍ አደረገ። ጠቅላላ ግምታቸው ከ126 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ መጻሕፍትን ነው ኢኒስቲትዩቱ ድጋፍ ያደረገው።

Pages