በዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ እና በሐሴዴላ ግቢ የተሰሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

ዲ,ዩ፦ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የከተማና መሰረት ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትርና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በተገኙበት፤ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል ነባር ህንፃዎች የሁለተኛ ዙር እድሳት የተጠናቀቁ እንዲሁም በሐሴዴላ ግቢ ዘመናዊ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ህንጻዎች ተመርቀዋል።
ኢንጂነር በፍቃዱ መኩሪያ፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ፤ በሁለቱም ጊቢዎች የተሰሩ የግንባታ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል

ዲ,ዩ፦ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 1829 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በድምቀት አስመርቋል።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር )፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች፣ ለተመራቂ ወላጆች እንዲሁም ለተማሪዎች ለምረቃ መብቃት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው፤ በተለይም ተመራቂዎች በዘንድሮ ዓመት በልዩ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የተሰጠውን የመውጫ ፈተና አልፈው የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ለምረቃ መብቃታቸውን አድንቀዋል።

"ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ቃል የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የችግኝ ተከላ አካሄደ

ዲ.ዩ፦ ሐምሌ 10/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በአገርአቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው "ነገን ዛሬ እንትከል" የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካል የሆነ የችግኝ ተከላ በዲላ ዩኒቨርሲቲ እፅዋት ጥበቃና ኢኮቱሪዝም ማዕከል ከማለዳ ጀምሮ ተከናውኗል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ጊዜያትም በደን ልማት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀው፣ በዛሬው እለት ከ17 ሽህ በላይ ችግኞችን በመትከል ላይ ነን ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ዩኒቨርሲቲው ቡና እና ቀርከሃን ጨምሮ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው 532 ሽህ ያህል ችግኞችን ቀድሞውኑ ለመትከል አቅዶ እየሰራ ነው ብለዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል በላብራቶሪ ዘርፍ የ"ISO" እውቅናን አገኘ

ዲ.ዩ፦ ሐምሌ 09/11/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል በቲቢ ምርመራ(Gene xpert) ላብራቶሪ ዘርፍ በISO የጥራት ደረጃ መዳቢ ድርጅት የእውቅና ሰርቴፍኬት ማግኘቱ ተገለጸ።
ዶ/ር ዘርሁን ተስፍዬ፣ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃም ተወካይ አንደገለፁት፤ ድርጅቱ በጤናው ዘርፍ በየስራ ክፍሉ ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት ያሟሉትን እውቅና እየሰጠ መምጣቱን አስታውሰው፤ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጂ ጠቅላላ ሆስፒታል በቲቢ ምርመራ (Gene xpert) ላብራቶሪ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ መዳቢ ከሆነው ISO እውቅና ማግኘቱን ገልጸዋል።

ለመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ተጠናቀቀ

ዲ.ዩ፦ ሐምሌ 07/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የመውጫ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲም የፈተናውን ደህንነትና ሚስጥራዊነት በማስጠበቅ እረገድ ትኩረት ሰጥቶ ከፀጥታ ግብረ-ኃይሉ ጋር በመቀናጀት ፈተናውን ሰጥቷል። ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መርሃግብር መሰረትም ከአንድ ሽህ 600 በላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከ870 በላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተናውን ተፈትነዋል።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር )፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፤ በዩኒቨርሲቲው በተዘጋጁ የፈተና ማዕከላት ከሰኔ 30 ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል።

በዲላ ዩኒቨርሲቲ እና በጣሊያኑ ቱሪን ዩኒቨርሲቲ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ገጽታ በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

ዲ.ዩ፦ ሐምሌ 4/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤትና የሀገረሰብ ጥናት ተቋም ከቱሪን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር፤ በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ያለውን የትብብር ስራ አሁናዊ ሁኔታ የተመለከተ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ ከሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ትብብር የተገኙ ልምዶች ተዳስሰዋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከጣልያኑ ቱሪን ዩኒቨርሲቲ ጋር በምርምር፣ "ስታፍ-ተማሪ" ልውውጥና ሌሎች አካዳሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ የትብብር ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

Pages